=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
.♥. አሰላሙ ዓለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ .♥.
አኽዋን ወል አኸዋት(ወንድም ና እህቶቼ) ዱዓ ላይ ያለን ግንዛቤ ምን ያህል ነው?
ዱዓ ላይ መበረታት ያስፈልጋል። ከአላህ እርዳታ እምንተይቅበት ብቸኛው መንገድም ነዉ። ቃለ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ ) የሰማይን በር ያንኳኳ ሳይከፈትለት አይቀርም ብለዋል። አዎ በመተናነስ ፣ ለሊት ላይ በመቆም ያ– አላህ ያ— ወዱድ ያ— ሙጂብ ብለን በሚወዳቸው 99 ስሞቹ እየተጣራን አልቅሰን በረቹን ስናንኳኳ አላህ የረህመት በሩን ይከፈፍትልናል።
አንድ ገጠሬ ወደ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) መጣና ያ ረሱለሏህ! ብሎ ጠራቸዉ እና ጥያቄውን እንዲህ በማለት ያቀርባል፦ ያ ረሱለሏህ ረበና(ጌታችን ቅርብ ነው እንመሳጠረዉ ወይስ እሩቅ ነዉ ጩኸን እንጥራው ያ አሏህ ብለን? ብሎ ጠየቃቸው። ረሱል መልስ አልሰጡም። አሏህ ግን ለዚህ ሰው ለጠየቀው ጥያቄ መለስ ሰጠ። መልሱም እንዲህ ይላል፦ ወ ኢዛ ሰአለከ ዒባዲ ዓኒ(ባሮቼ ስለኔ ጉዳይ ከጠየቁህ) ፈኢኒ ቀሪብ(እኔ ቅርብ ነኝ) ኡጂቡ ዳዕወተ ዳዒ ኢዛ ደዓ (እቀበላለው የተጣሪዎችን ጥሪ በጠሩኝ ግዜ እቀበላቸዋለው) በሚል የቁርኣን አያ አሏህ(ሱ.ወ) መልስ ሰጠ።
ስለዚህ አሏህ ለኛ ቅርብ ነው። ያሰበነውን እንዲሳካልን ከፈለግን ያለ መሰልቸት ደጋግመን የአሏህን እርዳታ እንጠይቅ።
:☀:.♥ ዱአ የሙስሊሞች ብቸኛው መሳሪያ ነው። ይህ መሳሪያ በችግር ጊዜም ይሁን በምቾት ጊዜ አንዲያገለግልህ የምትፈልግ ከሆነ ስለህ አስቀምጠው። ♥:☀:
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|